ኢንስቲትዩቱ የዝርያ ማሻሻያ ኮርማ መረጣ ጋይድ ላይን ላይ ምክክር አደረገ።
ህዳር 10/2017 እ.ል.ኢ
እንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የግብርና ሴክተር የሥራ ኃላፊዎች፣ አርቢዎችና ተመራማሪዎች የተሳተፉበት ምክክር በአዳማ አካሂዷል።
በዚህ የምክክር መድረክ ለሰው ሠራሽ ማዳቀል አገልግሎት የሚውለውን አባለ ዘር ለመሰብሰብ የሚውሉ ኮርማዎች መረጣ ጋይድ ላይን በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች በዝርዝር ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ እውቅ ምሁራን ተሳትፈውበታል።
በእለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋ/ዳ/ር ዳኛቸው በየነ (ዶ/ር) በወተትና በስጋ ምርት የተሻለ ዝርያ ያላቸውን የእንስሳት ዝርያ በመለየት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችል ጋይድ ላይን መሆኑን በመግለጽ ኢንስቲትዩቱም የተሻሻሉ ዝርያዎችን በስፋት ከማፍራት አኳያ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የእንስሳት ዝርያ ኢንፎርሜሽን መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ በሱፍቃድ ጁፋር እንዳሉት ኮርማ የአንድ መንጋ ግማሽ መሆኑን ገልጸው አንድ ጥሩ ኮርማ በርካታ እንስቶችን የሚያዳቅል በመሆኑ አርቢው ለኮርማ መረጣው መረጃ ኖሮት የሚጠበቅበትን ለመወጣት የሚረዳው ነው ብለዋል። አያይዘውም የሀገር ውስጥ ዝርያ ብቻ በመጠቀም የወተትና ሥጋ ምርታማነትን ዝርያን መሻሻል አይቻልም ብለዋል። በመጨረሻም በጋይድ ላይ በተሰጠው ግብዓት ዳብሮ ሥራ ላይ እንዲውል በመስማማት የዕለቱ ሰብሰባ ተጠናቋል።