በኮርያ ልማት ድርጅት ኢትዮጵያ ዳይሬክተር እንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም
ዛሬ ነሐሴ 27/2016 እንስሳት ልማት እንስቲትዩት ለአዲሱ የኮርያ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ዳይሬክተር M.r Cho han deog እና ልዑካን የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም ተካሄደ።
በፕሮግራሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የእንስሳት ልማት እንስቲትዩት ዶ/ር አስራት ጤራ የተቋሙን ዝርዝር ተግባራትም ለዳይሬክተሩ እና ለቡድኑ ገልፀዋል።
ዶ/ር አስራት ጤራ ሀገርቱ 70 ሚልዮን በላይ የቀንድ ከብት ቢኖራትም በቁጥሩ ልክ ተጠቃሚ እንዳልሆነች ገለፁ።
የኮርያ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ (ኮይካ) ከእንስሳት ልማት እንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የተስማሙበት መካከል:-
– የወተት ማቀነባበሪያ ህንፃ በዘመናዊ መልክ የመገንባት ለስራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ ማሽኖችን ማስገባት፣
-ዘመናዊ የስልጠና አዳራሽ መገንባት ፣
-በወተት ዘርፉ ዙርያ ያሉት ባለሙዎች እና ለሚመለከታቸው ሁሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ : ክብሩ ታደሰ
ካሜራ ፡ ዞማነሽ ውድነህ