ዓላማ
[read more]የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የሀገራችንን እንስሳት ሀብት ዝርያ ምርታማነት፣ ምርት ልማት፣ ጥራትና የገበያ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ አካባቢያዊ ዘላቂነትንና ተደራሽነትን ባረጋገጠ መልኩ ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሀገር ብልጽግና የላቀ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማድረግ ነው፡፡
ተልዕኮ
[read more]የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዝርያን በጥናትና ምርምር በማሻሻል፣ በማባዛትና በማስረጽ፣ የዘርፉን ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ፣ በእንስሳትና እንስሳት ተዋፅኦ ምርትና መኖ ማቀነባበር ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች አቅም በመገንባት፣ በማማከር እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር፣ ኢንቨስትመንትና ገበያ እንዲስፋፋና እንዲቀላጠፍ በመደገፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በብዛትና በጥራት እንዲቀርቡ በማድረግ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ማሳደግ፡፡
ራዕይ
[read more]በ2022 ኢንስቲትዩቱ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና በእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ማቀነባበር የምርምር፣ የሥልጠና፣ የማማከር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የብቃት ማዕከል ሆኖ ማየት፣