About LDI
ዓላማ, ተልዕኮ, ራዕይ
ዓላማ
የኢንስቲትዩቱ ዓላማ የሀገራችንን እንስሳት ሀብት ዝርያ ምርታማነት፣ ምርት ልማት፣ ጥራትና የገበያ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ አካባቢያዊ ዘላቂነትንና ተደራሽነትን ባረጋገጠ መልኩ ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሀገር ብልጽግና የላቀ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማድረግ ነው፡፡
ተልዕኮ
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዝርያን በጥናትና ምርምር በማሻሻል፣ በማባዛትና በማስረጽ፣ የዘርፉን ዕውቀትና ክህሎት በማሳደግ፣ በእንስሳትና እንስሳት ተዋፅኦ ምርትና መኖ ማቀነባበር ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች አቅም በመገንባት፣ በማማከር እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር፣ ኢንቨስትመንትና ገበያ እንዲስፋፋና እንዲቀላጠፍ በመደገፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በብዛትና በጥራት እንዲቀርቡ በማድረግ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ማሳደግ፡፡
ራዕይ
በ2022 ኢንስቲትዩቱ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና በእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች ማቀነባበር የምርምር፣ የሥልጠና፣ የማማከር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የብቃት ማዕከል ሆኖ ማየት፣
የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር
የኢንስቲትዩቱ ሥልጣንና ተግባር
ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የእንስሳት ዝርያዎችን ለማሻሻል፣ ዘላቂ የዝርያ አቅርቦት ለማስፋፋትየእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና የምርት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያዎችን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚረዱ ጥናትና ምርምሮችን ያካሂዳል፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርም ይሠራል፤
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ሞዴል የምርት ማቀነባበሪያዎችን ያቋቁማል፤ በዘርፉ ያሉ አገር በቀል እውቀቶችን ይለያል፤
- እንዲሁም በምርት ማቀነባበር ላይ የተሰማሩ የግል ኢንቨስትመንቶች የምርምር ክፍሎች እንዲያቋቋሙ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ሁለገብ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ የፖሊሲ፣ የስትራቴጂ፣ የፕሮግራምና መርሐ ግብሮችን ሀሳብ ያመነጫል፤
- ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ፣ የእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ እና የእንስሳት እርባታ ግብዓቶችን ወደ ሀገር በማስገባት፣ በሀገር ውስጥም በማምረትና በማባዛት አገልግሎት ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ ግብዓቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለሚያስገቡ አካላት የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በሀገር አቀፍ ደረጃ የዝርያ ማሻሻያ እና የእንስሳት ምርት ማቀነባበርን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ይሠራል፣ እንዳስፈላጊነቱ ለክልሎች ድጋፍና ምክር ይሰጣል፤
- ለእንስሳት ዝርያ መሻሻል አስተዋጽዎ የሚያደርጉ የእንስሳት ብዜት ማዕከላትን ያቋቁማል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ በሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ዝርያ ማሻሻያና ብዜት ማዕከላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፣
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያና ብዜት መረጃ እና የምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ልማት አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ፣ የገበያ፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች መረጃዎችንና ዕውቀት ያሰባስባል፣ ይተነትናል፣ የመረጃ ቋት ያደራጃል፣ ድረ-ገጽ ያዘጋጃል፣ አመቺ በሆኑ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጫል፤
- ለእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበር የሚያግዙና ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የቴክኒክ፣ የቴክኖሎጂ፣ የግብይት፣ የሥራ አመራርና ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ የሚዘጋጁ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ይሰጣል፣ አውደ ጥናቶችን፣ ሲምፖዚዬሞችን፣ ሴሚናሮችንና የልምድ ልውውጦችን ያዘጋጃል፤
- ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ የምርት ማቀነባበር እና የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ተግባራትን ለመደገፍ እንዲቻል በቁርኝት መርሐ ግብር የአቅም ግንባታ ለማከናወን፣ ደረጃውን የጠበቀ ዝርያዎችና ዘር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትም ሆነ ለማስወጣት እና ውጤታማ የግብይት ሥርዓት እንዲዘረጋ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፤
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልን እና እንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበርን በተመለከተ በምርት ሂደት እቅድና በጥራት አጠባበቅ ላይ የናሙና ምርት ማምረቻና ላብራቶሪዎች በኢንስቲትዩቱ ውስጥ በማቋቋም ድጋፍና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና እንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበር ኢንቨስትመንትን የሚመለከቱ ሥራዎችን በአግባቡ መደራጀታቸውን ያረጋገጣል፤ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና እምቅ አቅሞችን ይለያል፣ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የሚስፋፉበትን ስልት ይቀይሳል፤
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፣ እንስሳት ምርትና ተዋጽኦ እና የመኖ ማቀነባበር ላይ ለሚሠማሩ ባለሀብቶች በቴክኖሎጂ መረጣ፣ በድርድር፣ በግንባታ፣ በተከላና በሙከራ ምርት የማማከርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና እንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበር ተግባራት ሊያፋጥኑና ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ የዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይለያል፣ ይቀምራል፣ያስፋፋል፣ ተግባራዊ ለማድረግም ድጋፍ ይሰጣል፤
- በተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፓርኮች ውስጥና በዙሪያው ባለሀብቶችና ህብረተሰብ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና ምርት ተዋጽኦ ማቀነባበር ተግባራት ላይ እንዲሠማሩ ያበረታታል፤ ወደ ሥራ የገቡትንም ይደግፋል፤
- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና እንስሳት ምርትና ተዋጽኦ ማቀነባበር ዘርፍ ታዳሽ የሀይል ምንጮችን እንዲጠቀም እና የአካባቢ ብክለት እንዳያስከትል የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሠረት ለሚሰጣቸው አገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
- የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤
ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
Objectives , Mission and Vision
Objective
The objective of the institute is to ensure equitable and environmentally sustainable breed productivity, product quality and market competitiveness of the livestock sector
so as to boost its contribution to the overall economic development and prosperity of the country.
Mission
To increase animal production and productivity, the Livestock Development Institute by improving animal breed through research, multiplication and dissemination; develop sectoral knowledge and skill, capacitate investors who are working on animal and animal products and animal feed, consult and transfer new technologies, support the expansion and efficiency of investment and market, providing standard and competitive products, to the local and foreign market in quantity and quality and ensuring the benefits of the society and increasing the country’s income from the sector.
Vision
By 2022, the Institute shall be Center of Excellence for research, capacity building, consultancy and technology transfer in animal genetic improvement and animal product processing.
Powers and duties the Institute
Powers and duties the Institute
The Institute shall have the following powers and duties:-
- undertake research and studies on livestock breed improvement so as to expand sustainable breed supply, livestock product and by-product processing; works towards technology transfer;
- establish model processing units; identify sectoral indigenous knowledge; renders technical support to livestock product and by-product private investments to establish research units of breed improvement and livestock product processing;
- generate ideas on policies, strategies, programs, and action plans that ensure the overall competiveness of breed improvement and livestock product processing;
- import, domestically produce and multiply quality and standardized inputs for breed improvement, livestock products and by-product processing and makes it available for use; provide technical support to importers;
- works together with stakeholders at national level on livestock breeding and livestock products processing; advise and support regions whenever necessary;
- establish, organize and lead animal breeding centers that contribute for genetic improvement; collaborate with other breed improvement and multiplication centers in the country;
- collect and analyse technological knowledge, market information, and investment data necessary for breed improvement and livestock product and by-product processing; develop database and webpages; desiminate information through appropriate media;
- provide practical focused trainings, workshops, symposia, seminars, and other tailor-made trainings on technical, technological, management and marketing issues that assists the development and competitiveness of the breed improvement and livestock product processing;
- works together with pertinent stakeholders on twinning capacity building programs, on importation and exportation of standard breeds and genetic materials and on establishment of effective market system so as to enable the livestock product processing and genetic improvement to attain international standard;
- provide support and advisory services to livestock breed improvement and livestock product processing on production process plan, and quality compliance by establishing sample production laboratories and model processing plant in the institute;
- in collaboration with other stakeholders, ensure proper organization of breed improvement and product processing investment activities, identify potential investment capacity of the sector, devise mechanism for proper investment promotion and work towards the effectiveness of the investments;
- advice and give technical support for investors who wish to engage in breed improvement, livestock product and product processing and livestock feed processing in the selection of technology, negotiation, construction, installation and product testing;
- identify, compile, scale up and support the implementation of internationally accepted best practices to speed up competitive breed improvement and product processing;
- encourage investors and societies to engage in livestock breed improvement and product processing and also support investors operating in and around the integrated agro-industry parks;
- provide technical support to breed improvement and livestock products processing sector to use renewable energy sources to minimize environmental pollution;
- charges for services rendered in accordance with the regulation of the Council of Ministers;
- own property, enter into contracts, sue and be sued in its own name;
perform other related activities necessary for the attainment of its objective